በሶሻል ሚዲያ ላይ የሚተዋወቁት የሪል እስቴት ቤት ሽያጭ ማስታወቂያዎች ምን ያህል ይታመናሉ?
በምን መስፈርትስ ትክክለኛውን ማረጋገጥ እችላለሁ?
ከላይ ላነሳናቸው ጥያቄዎች የሁለቱን ጥያቄዎች ተመጣጣኝ መልሶች እነሆ።
ሀ/ ገንቢዉ የገነባዉ ቤት ካርታዉ በማን ስም ነዉ ብለን ጠይቀን ነበር። ካርታዉ በሚሸጠዉ ሪል እስቴት ስም ካልሆነ ልታገድ ወይም በባንክ የተያዘ ወይም በማናቸዉም ሁኔታ የኔ ነዉ ባይ ሊቀርብ ስለሚችል ለሽያጩ የሚቆረጠዉ ደረሰኝና ካርታ ፍጹም አንድ አይነት መሆን አለባቸዉ። ካልሆነ ገዥዉ ችግር ዉስጥ ሊገባ ይችላል።
ለ/ ገንቢዉ ለሚሸጠዉ ቤት ወዲያዉ የቫት ደረሰኝ መቁረጥ ይችላል? ብለን ጠይቀናል። የቫት ደረሰኝ ለጊዜዉ አልደረሰልኝም ወይም በዉል ብቻ ነዉ አሊያም በሌላ ምክንያት ደረሰኝ የለኝም የሚል ከሆነ የሪል እስቴት ፈቃድ የለዉም ማለት ነዉ። ይህ ደግሞ ኪሳራ ያስከትላል።
ሌሎች ጥያቄዎች በሚቀጥለዉ ይብራራሉ።